ወሎ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ ሙያ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ወሎ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ እና ሁለተኛ ድግሪ በተለያየ ሙያ ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 320 ተማሪዎች አስመረቀ፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አወል ሰይድ (ዶ/ር) በምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ፤ ዩኒቨርሲቲው በመማር ማስተማር፣ በምርምር ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በማሕበረሰብ አቀፍ ዘርፎች በርካታ ተግባራት ማከናወኑን አንስተዋል፡፡
በዩኒቨርሲቲው የመውጫ ፈተና ከወሰዱት መካከልም 80 ከመቶ ያህሉ ከ50 በመቶ በላይ ማምጣታቸውን ተናግረዋል፡፡
ተመራቂዎቹ በሰለጠኑበት የሙያ መስክ ሀገራቸውን እና ሕዝባቸውን በታማኝነት እንዲያገለግሉም አሳስበዋል፡፡
ዛሬ ካስመረቋቸው ተማሪዎች መካከልም 317 ያህሉ ሴቶች መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
በእሸቱ ወ/ሚካኤል