Fana: At a Speed of Life!

ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በነጋሶ ጊዳዳ ልዩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝተው ተማሪዎችን አበረታቱ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በደምቢዶሎ ከተማ ነጋሶ ጊዳዳ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝተው ተማሪዎችን አበረታቱ፡፡

በዚሁ ጊዜ፤ ተማሪዎች ኩረጃና ስርቆት የሚጠየፉ፣ በራሳቸው የሚሠሩና ጊዜያቸውን በአግባቡ የሚጠቀሙ እንዲሆኑ መክረዋል፡፡

ተማሪዎች ወደፊት የሚገጥማችሁ ዓለም ትልቅ እውቀት የሚፈልግ መሆኑን አውቃችሁ መዘጋጀት ይጠበቅባችኃል ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር አማካኝነትም ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እየተገነቡ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ተማሪዎች ጠንክረው በመማር ወደፊት ሀገራቸው ራሷን የቻለች፤ ለሌላ ሀገር የምትተርፍ እንድትሆን እንደሚያደርጓት እምነት እንዳላቸውም ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.