Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ድሮን ለውጭ ገበያ ማቅረብ የሚያስችል አቅም ገንብታለች- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ድሮን አምርቶ ከመጠቀም ባሻገር ለውጭ ገበያ ማቅረብ የሚያስችል አቅም መገንባቷን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሲቪልና ወታደራዊ አገልግሎት የሚውሉ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን (ድሮን) የሚያመርተውን የስካይ ዊን ኢንዱስትሪን መርቀው ከፍተዋል።

ኢንዱስትሪው ኢትዮጵያ በጸጥታና ደኅንነት ዘርፍ በቴክኖሎጂ ራሷን ለመቻል የጀመረችው ጥረት አካል መሆኑንም በዚሁ ጊዜ ተናግረዋል፡፡

ኢንዱስትሪው የሚያመርታቸው ድሮኖች ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን የመጠበቅ አቅሟን ይበልጥ የሚያሳድጉ መሆናቸውንም አስረድተዋል፡፡

ድሮኖቹ በከፍተኛ መልካዓ-ምድር ላይ በብቃት አገልግሎት የሚሰጡና ጸረ-ድሮን ጭምር የታጠቁ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል፡፡

አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጠቀሙም ነው የተናገሩት፡፡

ድሮኖቹ መረጃ ለመሰብሰብ፣ ለመከላከል አቅም እንዲሁም ለማጥቃት እንደሚውሉ ጠቅሰው፤ ኢንዱስትሪው ድሮኖችን ከኢትዮጵያ ባሻገር ለውጭ ገበያ ማቅረብ የሚያስችል አቅም እንዳለው አስታውቀዋል፡፡

በቀጣይም በዘርፉ የሚሠሩ ተቋማት ይበልጥ በመቀናጀት የምርምር ሥራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል፡፡

በምስክር ስናፍቅ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.