አባ ገዳ ጉዮ ቦሩ ጉዮ 72ኛው አባ ገዳ ሆነው ተሰየሙ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አባ ገዳ ኩራ ጃርሶ ስልጣናቸውን ለተከታያቸው በሰላም አስረክበዋል።
ተከታዩ አባ ገዳ ጉዮ ቦሩ ጉዮ 72ኛው አባ ገዳ በመሆን ለቀጣይ ስምንት ዓመታት ስልጣናቸውን በሰላም ተረክበዋል።
አባ ገዳ ኩራ ጃርሶ 71ኛው አባ ገዳ ሆነው ላለፉት ስምንት ዓመታት ሥርዓቱን በመምራት አገልግለዋል።
72ኛው አባ ገዳ ሆነው የተመረጡት አባ ገዳ ጉዮ ቦሩ ጉዮም ለሚቀጥሉት ስምንት ዓመታት የገዳውን ሥርዓት በበላይነት የሚመሩ ይሆናል።