Fana: At a Speed of Life!

ለሀገራችን ዕድገትና ብልጽግና እስካሁን ባገኘናቸው ስኬቶች ሳንረካ ሌት ተቀን መስራት አለብን – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለሀገራችን ዕድገትና ብልጽግና እስካሁን ባገኘናቸው ስኬቶች ሳንረካ ሌት ተቀን መሥራታችንን መቀጠል ይገባናል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ትናንት የተመረቀውን ለሲቪልና ወታደራዊ አገልግሎት የሚውሉ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን የሚያመርተውን የስካይ ዊን ኢንዱስትሪ አስመልክተው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም “ሁላችንም በተሰማራንበት ዘርፍ ለሀገራችን ዕድገት እና ብልጽግና እስካሁን ባገኘናቸው ስኬቶች ሳንረካ ሌት ተቀን መሥራታችንን መቀጠል ይገባናል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

“ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፍ ራሷን እንድትችል አቅደን እየሠራን ነው” ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ ተግባሩ ባልተጠበቀ ፍጥነት ስኬት እያመጣ መሆኑን ጠቁመዋል።

ለእስካሁኑ ስኬቶቻችን እና አስገራሚ ውጤቶች ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ደስ አለን ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.