በስልጣን ዘመኔ የሕዝብ አንድነት እንዲጠናከር እሰራለሁ – አባ ገዳ ጉዮ ቦሩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አባ ገዳ ጉዮ ቦሩ 72ኛው አባ ገዳ ሆነው በመሰየም ከ71ኛው የቦረና አባ ገዳ ኩራ ጃርሶ ስልጣናቸውን በዛሬው ዕለት ተረክበዋል፡
በርክክብ ሥነ ሥርዓቱ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች እንዲሁም የኬንያ ልዑካን ቡድን አባላት ተገኝተዋል፡፡
አባ ገዳ ጉዮ ቦሩ በዚህ ወቅት÷በስልጣን ዘመናቸው የሕዝቦች አንድነት እንዲጠናከር እና ሰላም እንዲሰፍን አበክረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም በመሰረተ ልማቶች መስፋፋት እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ በትኩረት እንደሚሰሩ መናገራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
72ኛው አባ ገዳ ጉዮ ቦሩ ለሚቀጥሉት ስምንት ዓመታት የገዳን ሥርዓት በበላይነት የሚመሩ ይሆናል።