የኩባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኩባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሩኖ ኤድዋርዶ ሮድሪጌዝ ፓሪላ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ሚኒስትሩ በአዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታ ከመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።