Fana: At a Speed of Life!

የከተማ የልማታዊ ሴፍትኔትና የሥራ ፕሮጀክት ተጠቃሚዎች ፕሮግራም ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ 154 ሺህ 923 ለተለያዩ ማኅበራዊ ችግሮች ተጋላጭ ወገኖችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የከተማ የልማታዊ ሴፍትኔት እና የሥራ ፕሮጀክት ተጠቃሚዎች ፕሮግራም ተጀመረ።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር ዓባይ ፕሮግራሙን በከተማ ደረጃ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አስጀምረዋል፡፡

በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግርም፤ ፕሮግራሙ ለሦስተኛ ዙር በከተማው እንደሚካሄድ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ቀደም ሲል በተካሄዱ ሁለት ዙር የልማት ሴፍትኔት ፕሮግራሞች ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደረጉ ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል ብለዋል፡፡

ዛሬ በተጀመረው የከተማ የልማታዊ ሴፍትኔት እና የሥራ ፕሮጀክት ላይ የሚሳተፋ ነዋሪዎች ውጤታማ እንዲሆኑ የተጠናከረ ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግም አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.