የሰላም መደፍረስ እንዳይኖር እየተሠራ ባለው ሥራ የሕዝቡ ሚና የላቀ ነው- አቶ ጥላሁን ከበደ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሰላም መደፍረስ እንዳይኖር እየተሠሩ በሚገኙ ሥራዎች ሂደት የሕዝቡ ሚና የላቀ መሆኑን ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ አስገነዘቡ፡፡
የክልሉ የፀጥታ ምክር ቤት 2ኛ ዓመት መደበኛ ጉባዔ በወላይታ ሶዶ ከተማ ተካሂዷል፡፡
ርዕሰ መሥተዳድሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ክልሉን የሰላም እና የመቻቻል ተምሳሌት ለማድረግ በተጀመረው ሥራ የፀጥታው ምክር ቤት አባላት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክተዋል፡፡
የመድረኩ ዓላማ በክልሉ የተሠሩ የፀጥታ ሥራዎችን በመገምገም ጥንካሬውን ለማስቀጠል እና ጉድለቶችን ለማረም መሆኑን የርዕሰ መሥተዳድር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡
በክልሉ የሰላም መደፍረስ እንዳይኖር በርካታ ሥራዎች መሠራታቸውን የጠቀሱት አቶ ጥላሁን፤ ለዚህም የሕዝቡ ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል።