ክልሉ የተመረቱለትን ሃምሳ ዋይ ቲኦ ትራክተሮች፣ ማረሻና መከስከሻዎች ለመረከብ ያለመ ምክክር አደረገ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ እና ሶማሌ ክልል በግብርና መሣሪያዎች አቅርቦት ላይ በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ውይይት አካሄዱ፡፡
በውይይቱ ላይ የኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ እና የሶማሌ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ ተገኝተዋል፡፡
ግሩፑ እና ክልሉ ከዚህ ቀደም በተስማሙት መሠረት፤ ሃምሳ ዋይ ቲኦ ትራክተሮች፣ ማረሻና መከስከሻዎች የተመረቱላቸው መሆኑን ተከትሎ እርክክብ ለማካሄድ ተስማምተዋል፡፡
በተጨማሪም 36 ትራክተሮች፣ ማረሻ እና መከስከሻዎች እንዲመረትለት ክልሉ ማዘዙን የግሩፑ መረጃ አመላክቷል፡፡
በቀጣይም የግብርና ቴክኖሎጂ ውጤቶች የሆኑ ምርቶችን ለመግዛት ፍላጎት እንዳለው ገተገልጿል፡፡