Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል ሕዝብ ሰላሙን የሚያውክ ኃይል አይፈልግም- አቶ አብዱልቃድር ረሺድ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሶማሌ ክልል ሕዝብ ወደ ጫካ ተመልሶ ሰላሙን የሚያውክ ኃይል አይፈልግም ሲሉ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አብዱልቃድር ረሺድ ገለፁ።

የክልሉ ሕዝብ ለዘመናት ያነሳቸው የነበሩት የልማትና የሰላም ጥያቄዎች ባለፉት የለውጥ ዓመታት መመለሳቸውን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

ይህን ሰላም ለማደፍረስ የተለያዩ ኃይሎች የሚያሰራጩትን የፀረ ሰላም መልዕክት የክልሉ ሕዝብና መንግሥት እንደማይታገሱ ማረጋገጣቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

የተፈቀደው የትግል ዓይነት ሰላማዊ ትግል ብቻ መሆኑን አስረድተው፤ ከዚህ ውጭ ወደ ጫካ ተመልሶ የሚደረግ ትግል እንደሌለና የሶማሌ ክልል ሕዝብም ይህን እንደማይፈልግ አስገንዝበዋል፡፡

ሰላማዊ በሆነ መልኩ የፖለቲካ አቋማቸውን ለማራመድ የተመዘገቡ ቡድኖችም፤ የሕዝቡን ሰላም በማያውክ መንገድ በመንቀሳቀስ አብሮነትን ከሚሸረሽሩ እንቅስቃሴዎች መቆጠብ አለባቸው ብለዋል።

በሌላ በኩል የክልሉ ሕዝብ ከቀናት በኋላ የሚከበረውን የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም ለማክበር ሕዝቡ ከፀጥታ አካላት ጋር በቅርበት እየሠራ እንደሚገኝ ገልፀው፤ እንደተለመደው ይህንኑ ትብብሩን እንዲያጠናክር ጠይቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.