Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ከተባበሩት መንግስታት የፕሮጀክት አገልግሎት ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ከተባበሩት መንግስታት የፕሮጀክት አገልግሎት ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ጆርጅ ሞሪኤራ ዳ ሲልቫ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ታዬ በውይይቱ ወቅት÷ ጽሕፈት ቤቱ የኢትዮጵያ መንግስት በሚያከናውናቸው በተለያዩ የግዢ ሂደቶች ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስራዎችን እንዲሰራ ጠይቀዋል፡፡

ጽሕፈት ቤቱ በአፍሪካ ውስጥ በሚያከናውናቸው የተለያዩ ፕሮጀክቶች ኢትዮጵያውያን ዕቃ አቅራቢዎችን እንዲያሳትፍና ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ጽሕፈት ቤት እንዲያስፋፋም ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

የጽሕፈት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ጆርጅ ሞሪኤራ ዳ ሲልቫ በበኩላቸው÷ ከፕሬዚዳንቱ ጋር ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸው፤ ጽሕፈት ቤቱ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር እንደሚፈልግም ጠቁመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.