Fana: At a Speed of Life!

በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት 12 ተቋማት አገልግሎት እየሰጡ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በአንድ ጣራ ስር 12 ተቋማት 41 አገልግሎቶችን እየሰጡ መሆናቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከልን በዛሬው ዕለት መርቀዋል፡፡
የአሰራር ስርዓቱ ዜጎች የተሟላ የዲጂታል አማራጮችን በመጠቀም በቀላሉ የተለያዩ የፌደራል ተቋማትን አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ገልጿል።
በማዕከሉ የሚሰጡ አገልግሎቶች ባለጉዳዮች ወደተለያዩ ቢሮዎች የሚያደርጉትን ምልልስ፣ረጅም የወረፋ ጥበቃና ከወረቀት ጋር ተዛማጅ የሆኑ ስራዎችን እንደሚያሰቀር ተገልጿል።
አሁን ሥራ ለጀመረው የሙከራ ፕሮጀክት በአጠቃላይ በፓይለት ፕሮግራም 12 የፌደራል መንግስት ተቋማት 41 የህዝብ አገልግሎቶችን እያቀረቡ እንደሆነም ጽ/ቤቱ ጠቁሟል፡፡
ከተቋማቱ መካከል የገቢዎች ሚኒስቴር የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ የብሄራዊ መታወቂያ አገልግሎት፣ የኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት ይገኙበታል፡፡
በተጨማሪም የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት፣ የትምህርት ምዘናና ፍተናዎች አገልግሎት፣ ኢትዮ ፖስታ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮ ቴሌኮም በማዕከሉ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡
ተቋማቱ በቴክኖሎጂ አማካኝነት በትስስር አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.