Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ቻይና በብሪክስ ማዕቀፍ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም ለሀገራቱ ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂካዊ አጋርነት አጽንኦት በመስጠት በሁለትዮሽና የባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
ሁለቱ ወገኖች በብሪክስ የትብብር ማዕቀፍ የሀገራቱን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር መስማማታቸውንም በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡
ውይይቱ በብራዚል ሪዮ ዴ ጄኖሮ እየተካሄደ ከሚገኘው የብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ጎን ለጎን ነው የተደረገው፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.