Fana: At a Speed of Life!

በሻንጋይ ዳይመንድ ሊግ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃን ያዙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቻይና ሻንጋይ በተካሄደው የወንዶች የ5 ሺህ ሜትር ውድድር አትሌት በሪሁ አረጋዊ አሸንፏል፡፡

አትሌቱ ርቀቱን በ12 ደቂቃ 50 ሰከንድ ከ45 ማይክሮ ሰከንድ በማጠናቀቅ ነው ቀዳሚ የሆነው፡፡

ሌላኞቹ ኢትዮጵያውያን አትሌት ኩማ ግርማ እና አትሌት መዝገቡ ስሜ ደግሞ በቅደም ተከተል 2ኛ እና ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቀዋል፡፡

በተመሳሳይ በሴቶች የ800 ሜትር ውድድር በሻንጋይ ዳይመንድ ሊግ በተደረገ የሴቶች 800 ሜትር አትሌት ጽጌ ዱጉማ  ምርጥ ሰአት በማስመዝገብ አሸንፋለች።

ጽጌ ርቀቱን ለማጠናቀቅ 1 ደቂቃ 56.64 ሰከንድ ወስዶባታል። ይህም የኢትዮጵያን የርቀቱ ክብረ ወሰን እድታሻሽል አስችሏታል።

ንግስት ጌታቸው እና ሀብታም አለሙ 6ኛ እና 8ኛ በመውጣት ውድድራቸውን አጠናቀዋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.