Fana: At a Speed of Life!

የሀገርን ዳር ድንበር ክብርና ሉዓላዊነት የሚያስጠብቅ ብቁና ጠንካራ ሰራዊት ተገንብቷል- ሌ/ጀ መሐመድ ተሰማ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሀገርን ዳር ድንበር ክብርና ሉዓላዊነት የሚያስጠብቅ ብቁና ጠንካራ ሰራዊት ተገንብቷል ሲሉ የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል መሐመድ ተሰማ ገለጹ።

ከክፍለ ጦር እስከ ጓድ ያሉ የምስራቅ እዝ አመራሮች የመሪነት ሚና እና ተያያዥ ወታደራዊ አቅሞችን የሚያጎለብቱ ስልጠናዎችን በብርሸለቆ መስረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ት/ቤት ለወራት ተከታትለው አጠናቅቀዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት ሌተናል ጀነራል መሐመድ ተሰማ÷ የሀገርን ዳር ድንበር  ክብርና ሉዓላዊነት የሚያስጠብቅ ብቁና ጠንካራ ሰራዊት መገንባቱን ገልጸዋል።

የሰራዊቱ አመራሮች ብቃት በተለያዩ ወታደራዊ እውቅቶችና ቴክኖሎጂዎች በመገንባቱ በየትኛውም ግዳጅና ተልእኮ በብቃት የመምራትና የመፈጸም አቅም በአስተማማኝ መልኩ ተገንብቷል ነው ያሉት።

እንደ አጠቃላይ የሰራዊቱ ጀግንነት፣ የመፈፀም አቅምና የሀገር ሉዓላዊነት የመጨረሻ ምሽግ በመሆን አስተማማኝ ቁመና ላይ የሚገኝ መሆኑን አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያን ሰላምና እድገት የማይፈልጉ የውጭና የሀገር ውስጥ ጠላቶች መኖራቸውን አንስተው÷ በየትኛውም መልኩ የሀገሩን ሰላምና ሉዓላዊነት በጀግንነት ማስከበር የሚችል ሰራዊት እንደተገነባ መናገራቸውን ኢዜአ ነው የዘገበው፡፡

ሀገር የማፍረስ አላማ በመያዝ በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሰውን ጽንፈኛ ሃይል ላይ ጠንካራ ርምጃ በመውሰድ እቅዱን ማክሸፍ መቻሉንም አብራርተዋል።

የአመራር ኮርሱን የወሰዱት ወታደራዊ አመራሮችም ከመቼውም ጊዜ በላይ በጀግንነት የሀገርን ክብር፣ ሉዓላዊነትና አንድነት ለማስጠበቅ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.