Fana: At a Speed of Life!

ቼልሲ ከሊቨርፑል የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ35ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ቼልሲ በስታምፎርድ ብሪጅ ሊቨርፑልን የሚያስተናግድበት ጨዋታ ይጠበቃል።
ለቀጣይ ዓመት የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ እየተፎካከሩ የሚገኙት ሰማያዊዎቹ ምሽት 12:30 የሊጉ ሻምፒዮን መሆኑን ካረጋገጠው ሊቨርፑል ጋር ይጫወታሉ።
በጨዋታው መጀመሪያ ላይ የቼልሲ ተጫዋቾች ለሊጉ ሻምፒዮን ሊቨርፑል የክብር አቀባበል እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡
ከዚህ ጨዋታ አስቀድሞ ቀን 10 ሰዓት ማንቼስተር ዩናይትድ ከሜዳው ውጭ ብሬንትፎርድን ይገጥማል።
ሌላኛው ለአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ እየተፎካከረ የሚገኘው ኒውካስል ዩናይትድ ከሜዳው ውጭ ብራይተንን የሚገጥም ሲሆን፥ ዌስትሃም ከቶተንሃም ከቀኑ 10 ሰዓት የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.