Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች ለአርበኞች ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች ለ84ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን የእንኳን አደረሳችሁ የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ኤምባሲዎቹ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የኢትዮጵያ አርበኞች ለሀገራቸው ነጻነት እና ክብር የከፈሉትን መስዋዕትነት አድንቀዋል፡፡

በዛሬው ዕለትም ከኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ዕለቱን ማሰባቸውን አስታውቀው፤ ሰላም እና ብልጽግናን ተመኝተዋል፡፡

የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት ካስተላለፉት መካከልም፤ በኢትዮጵያ የካናዳ፣ ሩሲያ፣ አውስትራሊያ፣ አሜሪካ፣ ሲሪላንካ እና የኢራን ኤምባሲዎች ይገኙበታል፡፡

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች፣ አርበኞች፣ የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች እና የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች በተገኙበት 84ኛው የጀግኖች አርበኞች የድል ቀን አራት ኪሎ በሚገኘው የድል ሐውልት ዐደባባይ ተከብሯል፡፡

በዚሁ ወቅት ፕሬዚዳንት ታዬ ባደረጉት ንግግር፤ የአርበኞች ቀን (የድል ቀን) የቅኝ ግዛት እሳቤ በአፍሪካ ምድር መሸነፍ እንደሚችል ዳግም የተገለጠበት ብርቱ የተጋድሎ መገለጫ ነው ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.