የፓኪስታንና አፍሪካ የንግድ ልማት ጉባኤና አውደ – ርዕይ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው
አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ – የፓኪስታን ንግድ ልማት ባለስልጣን (TDAP) እና የፓኪስታን ንግድ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የፓኪስታን ኤምባሲ የንግድ ክፍል ጋር በመተባበር 5ኛው የፓኪስታንና አፍሪካ የንግድ ልማት ጉባኤ (PATDC) እና የፓኪስታን ምርቶች ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ፣ በሚሊኒየም አዳራሽ ከግንቦት 7 – 9፣ 2017 ድረስ ሊያካሂዱ መሆኑን አስታወቁ።
ይህ የሶስት ቀናት ኹነት በፓኪስታን እና በአፍሪካ መካከል የንግድና ኢንቨስትመንት እድሎችን ለመፍጠር የተዘጋጀ ነው። ጉባኤው የአፍሪካ እና የፓኪስታን ከፍተኛ የመንግስት ልዑካን፣ የንግድ መሪዎች፣ ባለሀብቶችና ባለሙያዎች የሚሳተፉበት ይሆናል።
በኤግዚቢሽኑ ላይ የፓኪስታን ኩባንያዎች የተለያዩ ምርቶቻቸውንና አገልግሎቶቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን ከነዚህም መካከል መድኃኒቶች፣ የህክምና መሣሪያዎች፣ አልባሳት፣ የምግብ ምርቶች፣ የውበት መጠበቂያዎች እና ሌሎችም ይገኙበታል።
ኹነቱ በንግድ ልማት ላይ ያተኮሩ የተለያዩ ዝግጅቶችን የሚያካትት ሲሆን ከእነዚህም መካከል የንግድ ጉባኤ፣ የሁለትዮሽ የንግድ ውይይቶች (B2B)፣ የመንግሥታት ውይይቶች (G2G) እና የእራት ፕሮግራሞች ይገኙበታል።
የፓኪስታን ንግድ ሚኒስቴር እንደገለጸው፣ ይህ ጉባኤ በፓኪስታን እና በአፍሪካ መካከል የንግድ ግንኙነቶችን ለማጠናከር ትልቅ ሚና ይጫወታል።
Pakistan-Africa Trade Development Conference and Exhibition to be Held in Addis Ababa!!
The Trade Development Authority of Pakistan (TDAP) and the Pakistani Ministry of Commerce, in collaboration with the Pakistani Embassy in Ethiopia commercial wing, have announced the 5th Pakistan-Africa Trade Development Conference (PATDC) and an exhibition of Pakistani products will be held in Addis Ababa at the Millennium Hall from May 15th – 17th, 2025.
This three-day event is designed to create trade and investment opportunities between Pakistan and Africa. The conference will be attended by high-level government delegations, business leaders, investors, and experts from Africa and Pakistan.
At the exhibition, Pakistani companies will showcase their diverse products and services, including pharmaceuticals, medical equipment, textiles, food products, beauty supplies, and more.
The event will feature various activities focused on trade development, including a business conference, bilateral business-to-business (B2B) meetings, government-to-government (G2G) discussions, and dinner programs.
According to the Pakistani Ministry of Commerce, this conference will play a significant role in strengthening trade relations between Pakistan and Africa.