Fana: At a Speed of Life!

ከ4 ሺህ ኪሎ ግራም በላይ የወርቅ ምርት ለብሔራዊ ባንክ ገቢ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፉት ዘጠኝ ወራት 4 ሺህ 254 ኪሎ ግራም የወርቅ ምርት ለብሔራዊ ባንክ ገቢ ማድረጉን የጋምቤላ ክልል ማዕድን ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

1 ሺህ 850 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ገቢ አቅደው እንደነበር የኤጀንሲው ምክትል ዳይሬክተር ኤልያስ ገዳሙ አስታውሰዋል፡፡

ይሁን እንጂ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ሕገ ወጥ የወርቅ ግብይትን በመቀነስ ወደ ብሔራዊ ባንክ የሚገባው የወርቅ መጠን እንዲጨምር ማድረጉን ነው ያነሱት፡፡

በተጨማሪም መንግሥት ለማዕድን ዘርፉ የሰጠው ልዩ ትኩረት ውጤት ማምጣቱን አስረድተዋል፡፡

ዲማ፣ አቦቦ፣ ጋምቤላ እና መንገሺ ወረዳዎች በክልሉ የወርቅ ምርት በስፋት እንደሚመረትባቸው ይታወቃል፡፡

በአብዱ መሀመድ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.