Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል በ2017/18 የመኸር ወቅት ከ360 ሚሊየን በላይ ኩንታል ምርት ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2017/18 የምርት ዘመን በሰብል ከሚሸፈነው ከ11 ሚሊየን ሔክታር በላይ መሬት ከ360 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ ጌቱ ገመቹ ገለጹ፡፡

በክልል ደረጃ በአርሲ ዞን ሄጦሳ ወረዳ ሻቂ ሸረራ ቀበሌ የመኸር እርሻ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሂዷል።

አቶ ጌቱ በዚሁ ወቅት እንደክልል በአጠቃላይ ከሚለማው መሬት 80 በመቶው በኩታ ገጠም እንደሚታረስ፤ 42 በመቶ መሬት ደግሞ በሜካናይዜሽ ታግዞ እንደሚለማ ተናግረዋል፡፡

በክልሉ ዘንድሮ በአርሶ አደሩ የተገዙ ትራክተሮችን ጨምሮ 10 ሺህ ትራክተሮች የግብርና ልማት ሥራውን እያሳለጡ መሆኑንም አስረድተዋል።

ከ10 ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ለመኸር እርሻ ለማቅረብ እየተሠራ መሆኑን ጠቅሰው፤ እስከ አሁን ከ5 ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ እየተሰራጨ ይገኛል ብለዋል።

በሚስሩ ቱሪ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.