Fana: At a Speed of Life!

የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፈተናዎችን በማረም ምቹ መደላድል ተፈጥሯል – ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ሂደት ላይ የነበሩ ፈተናዎችን በማረም በዘርፉ ምቹ መደላድል መፍጠር ተችሏል ሲሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ገለጹ።

3ኛው “ኢንቨስት ኢትዮጵያ 2025” ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በፎረሙ ላይ እንደገለጹት፤ ባለፉት ዓመታት እድገትን ለማስቀጠል፣ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን ለመሳብና መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችሉ ማሻሻያዎች ተደርገዋል።

ይህም ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ካላት ምቹ አቅም ጋር ተዳምሮ ሀገሪቱን ተመራጭ እንድትሆን ያደርጋታል ብለዋል።

ኢትዮጵያ በ2030 ከአፍሪካ በምጣኔ ሀብቷ ቀዳሚ ለመሆን ራዕይ መያዟን ጠቅሰው፤ ለዚህ ያግዝ ዘንድ ለኢንቨስትመንት ዘርፍ መንግስት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሆነ አንስተዋል።

በውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ውጤት ለማምጣት በሶስት መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት መደረጉን ጠቁመው፤ ፖሊሲዎችን ምቹ ማድረግ፣ መሰረተ ልማቶችን ማስፋት እና ቀልጣፋ ግንኙነት እንዲኖር ማስቻል ዋና ዋና ነጥቦች መሆናቸውን ገልጸዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በፍጥነት እያደጉ ከሚገኙ 10 ሀገራት ተርታ እንደምትገኝ ገልጸዋል።

ከፍተኛ መጠን ያለው ወጣት የሰው ሃይል እንዳላት ጠቁመው፤ ለኢንቨስትመንት ምቹ መዳረሻ በሆነችው ኢትዮጵያ ባለሀብቶች ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አስተላልፈዋል።

በታምራት ደለሊ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.