Fana: At a Speed of Life!

የግብርናና ገጠር ልማት ፖሊሲው የዘርፉን አስተዋፅኦ ለማሳደግ ያስችላል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አዲሱ የግብርናና ገጠር ልማት ፖሊሲ የዘርፉን አስተዋፅኦ ለማሳደግ የሚያስችል መሆኑ ተገለጸ።

ለሐረሪ ክልልና ድሬዳዋ አስተዳደር ባለድርሻ አካላት የግብርናና ገጠር ልማት ፖሊሲ ማስተዋወቂያ መድረክ በሐረር ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የተገኙት የሐረሪ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሮዛ ኡመር፤ ፖሊሲው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል።

ሀገራዊ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የግብርና ዘርፍን ከሌሎች ዘርፎች ጋር የበለጠ ለማስተሳሰር እንደሚያስችል ገልጸዋል።

እንዲሁም የተፈጥሮ ሃብትን ለመጠበቅና በዘላቂነት ለመጠቀም ጉልህ ሚና እንዳለው ጠቅሰው፤ የግብርና ምርታማነትና ተወዳዳሪነትን ለማረጋገጥና የገጠር መዋቅራዊ ሽግግርን ለማሳካትና በኢኮኖሚው የግብርናውን ድርሻ ለማሳደግ እንደሚያስችል ጠቁመዋል።

የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ፖሊሲው ከዚህ በፊት ይስተዋሉ የነበሩ ችግሮችን በመፍታት ምርታማነት እንዲጨምር፣ የግሉ ዘርፍ እንዲበረታታና ዘመናዊነትን የሚያረጋግጥ ሆኖ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

ግብርናን ለምርታማነትና ለትርፋማነት እንዲውልና እድገት እንዲያስመዘግብ ትኩረት መሰጠቱንም ገልጸዋል፡፡

የግብርናና ገጠር ልማት ፖሊሲ በሚኒስትሮች ም/ቤት ጸድቆ ወደ ስራ እንዲገባ መደረጉ ይታወሳል።

በተሾመ ኃይሉ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.