ምክር ቤቱ አራት ስምምነቶችን አጸደቀ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 29ኛ መደበኛ ስብሰባው አራት የስምምነት አዋጆችን መርምሮ አጽድቋል።
በቀዳሚነት የጸደቀው ለአካባቢ እና አረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት በኢትዮጵያ እና በጣሊያን መንግስት መካከል የተደረገው የ11 ሚሊየን 500 ሺህ ዩሮ የብድር ስምምነት ነው።
ለመማር ማስተማር ማጎልበቻ የትምህርት ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም ማስፈፀሚያ የኢትዮጵያ መንግስት ከዓለም አቀፍ የልማት ማህበር ጋር ያደረገው የ50 ሚሊየን ዶላር የብድር ስምምነት ጸድቋል።
በተጨማሪም የአፍሪካ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን ማቋቋሚያ ስምምነት እንዲሁም በኢትዮጵያ እና በኦስትሪያ መንግስት መካከል የተፈረመው የትራንስፖርት ስምምነት ጸድቋል።
በፍቅርተ ከበደ