ድሬዳዋ ከተማ እና መቐለ 70 እንደርታ ነጥብ ተጋሩ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ29ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር የተገናኙት ድሬዳዋ ከተማ እና መቐለ 70 እንደርታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተለያይተዋል፡፡
የድሬዳዋ ከተማን ግብ ሀቢብ ከማል በፍጹም ቅጣት ምት በሁለተኛው የጨዋታ አጋማሽ ማስቆጠር ችሏል፡፡
እንዲሁም የመቐለ 70 እንደርታን ግብ ያሬድ ብርሃኑ ወደ መልበሻ ክፍል ከማምራታቸው በፊት ከመረብ ማሳረፍ ችሏል፡፡
የዕለቱ የመጨረሻ የጨዋታ መርሐ ግብር ሲቀጥል 12 ሠዓት ላይ፤ ሀድያ ሆሳዕና ከወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጋር ይገናኛሉ፡፡