Fana: At a Speed of Life!

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በአጭር ጊዜ ውስጥ ተስፋ ሰጪ ውጤት አስመዝግቧል – ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ የተተገበረው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተስፋ ሰጪ ውጤት ማስመዝገቡን ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ገለጹ።

የኢትዮጵያ የፋንናንስ ፎረም በዛሬው ዕለት የተጀመረ ሲሆን÷ በመድረኩ ላይ የተገኙት ፕሬዚዳንት ታዬ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ወደ መሬት በወረደ አጭር ጊዜ ውስጥ አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን ተናግረዋል።

ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ ዕድሜ ያለው የሀገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ የሚፈለገውን ያህል እድገት ሳያስመዘግብ መቆየቱን አንስተው÷ በዘርፉ የተጋረጡ መሰናክሎችን ለማለፍ አካታችና ዘመኑን የዋጀ ሥርዓት ለመፍጠር የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተግባራዊ መደረጉን አመላክተዋል።

በቀጣይም የሀገራችንን የፋይናንስ ዘርፍ ወደ ዲጂታል ለማሸጋገር ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

የፋይናንስ ፎረሙ የፋይናንስ ዘርፉን አንገብጋቢ ችግሮች ለመቅረፍ፣ የግሉን ዘርፍ ጥያቄ ወደ መድረክ ለማምጣት እና ለችግሮች ላይ የመፍትሄ ሀሳቦችን ለማዋጣት ጠቀሜታው የጎላ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

በፎረሙ ላይ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱን ጨምሮ የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የባንኮች ፕሬዚዳንቶች እና ከሀገር ውስጥ እና ከውጪ የተጋበዙ እንግዶች እየተሳተፉ ይገኛል።

በቃለአብ ግርማ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.