Fana: At a Speed of Life!

የባህር በር ጥያቄ መልስ እንዲያገኝ ሕዝቡ ተገቢውን ድጋፍና ርብርብ ማድረግ አለበት – ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ የታየውን ህዝባዊ ቁርጠኝነት በባህር በር ተጠቃሚነት ጥያቄ ላይ መድገም እንደሚገባ ምሁራን ተናግረዋል።

ምሁራኑ ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር በነበራቸው ቆይታ፥ የባህር በር ተጠቃሚነት ጊዜው የሚጠይቀው የህልውናና የብሄራዊ ጥቅም ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የፖለቲካ ተንታኙ ሴኔሳ ደምሴ፥ ህዝቡ የኑሮ ሁኔታው ሳይበግረው የግድቡን ግንባታ ከጫፍ ማድረስ እንደቻለው ሁሉ የባህር በር ጥያቄው መልስ እንዲያገኝ ድጋፍና ርብርብ ማድረግ እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

የዓለም አቀፍ ግንኙነትና ዲፕሎማሲ ባለሙያው ጥላሁን ሊበን በበኩላቸው፥ አንድነትን በማጠናከር በሰላማዊ መንገድ የባህር በር ጥያቄው የሚመለስበትን መንገድ ማመቻቸት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

የባህር በር ተጠቃሚነት ጥያቄ ብቻውን ግብ ሊሆን እንደማይችል የገለጹት ምሁራኑ፥ ዋና ግቡ የባህር በር ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

በመቅደስ ከበደ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.