Fana: At a Speed of Life!

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት በቨርቹዋል ባካሄደው 45ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
ምክር ቤቱ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
በቅድሚያ ምክር ቤቱ የተወያየው የባለብዙ ተዋንያን የግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎትና አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡
በሀገራችን ባለፉት ዓመታት የግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎት በመንግሥት ብቻ ሲሰጥ ቆይቷል፡፡
እያደገ ከመጣው የዘርፉ ፍላጎት አንፃር መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን፣ የግል ዘርፉን፣ የሕብረት ሥራ ማሕበራትንና የሙያ ማሕበራትን ማሳተፍ የሚያስችል የአሰራር ሥርዓት መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡
ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው የሥርዓተ ምህዳር አገልግሎት ክፍያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡
በሀገራችን የሥርዓተ ምህዳር ክፍያ አሰራርን የተመለከተ የህግ ማዕቀፍ ባለመኖሩ ወጥ ባልሆነ አሰራር በተለያዩ አካላት ሲተገበር ቆይቷል፡፡
አሁን በደረስንበት የእድገት ደረጃ የፌዴራል እና የክልል ተቋማት፣ የግሉ ዘርፍ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ከግምት ውስጥ ያስገባ የህግ ማዕቀፍ መኖር አስፈላጊ ይሆናል፡፡
ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.