Fana: At a Speed of Life!

በአፍሪካ ህብረት የሚደረጉ የባለ ብዙ ወገን ትብብሮች ለሰላም ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርገዋል – ፕሬዚዳንት ፑቲን

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአፍሪካ ህብረት እና ቀጣናዊ ተቋማት ማዕቀፍ ስር የሚደረጉ የባለ ብዙ ወገን ትብብሮች ለሰላምና መረጋጋት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርገዋል ሲሉ የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ገለጹ።

ፕሬዚዳንቱ የአፍሪካ ህብረት የተመሰረተበትን 62ኛ ዓመት አስመልከተው ለአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት የያዘ ደብዳቤ ልከዋል፡፡

በመልዕክታቸውም አፍሪካውያን ነፃነታቸው ከተረጋገጠ በኋላ ባለፉት ስድስት አስርት ዓመታት ራሳቸውን የዓለም ማህበረሰብ አካል በማድረግ በርካታ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ስኬቶችን ማስመዝገብ መቻላቸውን ገልፀዋል፡፡

በአፍሪካ ህብረት እና ቀጣናዊ ተቋማት ማዕቀፍ ስር የሚደረጉ የባለ ብዙ ወገን ትብብሮች ለአህጉሪቱ ሰላምና መረጋጋት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጋቸውንም ጠቅሰዋል፡፡

ሩሲያ ከአፍሪካ ጋር ያላት ወዳጅነት እና ትብብር ይበልጥ እንዲጠናከር መንግስታቸው ድጋፉን እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

የሩሲያ እና አፍሪካ ህዝብ ጥቅምን ያማከለ ፍትሃዊ እና ዴሞክራሲያዊ የሆነች ባለ ብዙ ዋልታ ዓለም ለመገንባት የሁለትዮሽ ትብብሩ የበለጠ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እምነታቸውን ገልፀዋል፡፡

በሚኪያስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.