የሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም የመቻል ግብ አርበኝነት ጥሪ ነው – ኮሚሽኑ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም የመቻል ግብ የአርበኝነት ጥሪ መሆኑን የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ።
የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ሥርዓት ግንባታ እና የሰብዓዊ ድጋፍ በራስ አቅም ንቅናቄ ስትራቴጂክ ማዕቀፎች ትግበራ ለፌዴራል፣ ክልል፣ ከተማ አስተዳደርና ባለድርሻ አካላት የተዘጋጀ የአቅም ግንባታ መድረክ መካሄድ ጀምሯል።
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም በዚሁ ወቅት÷ የሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመቻል የሚደረገው ጥረት በተግባር የሚረጋገጥ መሆኑን ገልጸዋል።
የተጀመሩ ተግባራትን በማጠናከር በ2018 ዓ.ም በራስ አቅም ራስን መቻል የሚለውን ተግባራዊነት ለማረጋገጥ እንደሚሰራ አንስተው÷ የሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም የመቻል ግብ የአርበኝነት ጥሪ መሆኑን አመላክተዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የካቢኔና የሴክተር ተቋማት ክትትል ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አክሊሉ ታደሰ በበኩላቸው÷ በደም የተከበረውን ሉዓላዊነታችንን፣ ክብራችንና ነፃነታችንን በላባችንን ማረጋገጥ አለብን ብለዋል።
ተፈጥሮ የቸረውን ፀጋ በቴክኖሎጂ በመታገዝ ከተረጂነት መውጣት እንደሚገባ ገልጸው÷ መንግሥት የታሪክ እጥፋት ለሆነው የሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራም ተናግረዋል።
በሰለሞን በየነ