Fana: At a Speed of Life!

ለሀገር ግንባታ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ሚና መጎልበት

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች በሀገር ልማት ላይ ያላቸውን የጎላ ሚና በመገንዘብ የሚጠበቅባቸውን እንዲያበረክቱ ተጠየቀ፡፡፡

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴዔታ ዴንጌ ቦሩ እንዳሉት፤ 86 በመቶው የኢትዮጵያ የወጪ እና ገቢ ንግድ የሚጓጓዘው በከባድ ተሽከርካሪዎች ነው፡፡

በመሆኑም የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች አቅርቦት በሚፈለግበት ጊዜና ቦታ በፍጥነት በማድረስ ያላቸውን የጎላ ሚና ተረድተው ሀገርን ወደፊት ለማራመድ መትጋት አለባቸው ነው ያሉት፡፡

እንደሀገር እና እንደ ዓርበኛ በማሰብ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት መወጣት እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል፡፡

የትራንስፖርት አገልግሎት በሎጂስቲክስ ሂደት ውስጥ መሠረታዊ የጀርባ አጥንት መሆኑን ያነሱት ደግሞ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አማካሪ መንግሥት ኃ/ማርያም (ዶ/ር) ናቸው፡፡

የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች በሚሰጡት አገልግሎት የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እና የሕብረተሰቡን የዕለት ተለት ኑሮ በመደገፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱም ተናግረዋል፡፡

በዮናስ ጌትነት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.