Fana: At a Speed of Life!

እስራኤል እና ሶሪያ በመካከላቸው ያለውን ውጥረት ለማርገብ መወያየታቸው ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) እስራኤል እና ሶሪያ በመካከላቸው ያለውን ውጥረት ለማርገብና በድንበር አካባቢ ያሉ ግጭቶችን ለማስቆም ያለመ የቀጥታ ውይይት መጀመራቸው ተነግሯል፡፡

ውይይቱ በመካከለኛው ምስራቅ ቀጣና ለዓመታት በተቃርኖ የቆዩት ሁለቱ ሀገራት ግንኙነታቸውን ለማደስ የሚያስችላቸው ወሳኝ ምዕራፍ ነው ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሁለት ሳምንታት በፊት በሳዑዲ አረቢያ ባደረጉት ይፋዊ ጉብኝታቸው ወቅት እስራኤል እና ሶሪያ ግንኙነታቸውን እንዲያድሱ ጠይቀው እንደነበር ይታወሳል፡፡

በተመሳሳይ የትራምፕ አስተዳደር እስራኤል በሶሪያ የምትፈጽማቸውን ጥቃቶች እንድታቆም ሲያሳስብ መቆየቱንም ዘገባው አስታውሷል፡፡

የሶሪያ ፕሬዚዳንት አህመድ አል ሻራ ከሳምንታት በፊት ሀገራቸው ከእስራኤል ጋር ያለውን ውጥረት ለማርገብ ቀጥተኛ ያልሆነ ድርድር እያደረገች መሆኑን ገልጸው ነበር፡፡

በቅርብ ጊዜያት የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት ፊት ለፊት ተገናኝተው ቀጥተኛ ድርድር ሲያደርጉ መቆየታቸውን ዘገባው አመልክቷል፡፡

በኃይለማርያም ተገኝ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.