በሶማሌ ክልል የዳያስፖራው የልማት ተሳትፎ እያደገ ነው
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሶማሌ ክልል በተያዘው የበጀት ዓመት 21 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሃብቶች ወደ ሥራ መግባታቸውን የክልሉ ኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪ ቢሮ አስታወቀ፡፡
የቢሮው ኃላፊ አሕመድ ረሻድ እንዳሉት፤ በተያዘው የበጀት ዓመት 19 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ 228 ፕሮጀክቶች ወደ ሥራ ገብተዋል፡፡
በተጨማሪ 1 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ 28 የዳያስፖራ ፕሮጀክቶች ወደ ሥራ መግባታቸውን ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡
ባለፉት 10 ወራት በአጠቃላይ 21 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ 256 ፕሮጀክቶች ወደ ሥራ መግባታቸውን ጠቅሰዋል፡፡
ኢንዱስትሪ፣ ሆቴል፣ ኮንስትራክሽን እና ጤና ፈቃድ የተሰጠባቸው ዘርፎች መሆናቸውንም አብራርተዋል፡፡
ፕሮጀክቶቹ ለ9 ሺህ 734 ወገኖች የሥራ ዕድል መፍጠራቸውንም አስረድተዋል፡፡
በአጠቃላይ በሶማሌ ክልል የዳስፖራው የኢንቨስትመንት ተሳትፎ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱንም ተናግረዋል፡፡
በዮሐንስ ደርበው