ኢትዮጵያ መድን ሲዳማ ቡናን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናከረ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ32ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን ሲዳማ ቡናን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል፡፡
የኢትዮጵያ መድንን የማሸነፊያ ግቦች ወገኔ ገዛኸኝ፣ አቡበከር ሳኒ እና ብርሃኑ በቀለ (በራስ ላይ) ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ መድን ወደ ድል ሲመለስ ሲዳማ ቡና ከተከታታይ ሶስት ጨዋታዎች ድል በኋላ ሽንፈት አስተናግዷል፡፡
ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ መድን በ63 ነጥብ ሊጉን ሲመራው ሲዳማ ቡና በ46 ነጥብ 4ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
የሊጉ ጨዋታ ሲቀጥል ምሽት 12 ሰዓት ላይ ባህር ዳር ከተማ ከአርባምንጭ ከተማ ይገናኛሉ፡፡