Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ 11 ሆቴሎች የባለ አምስት ኮከብ ደረጃ አገኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቱሪዝም ሚኒስቴር ባካሄደው የደረጃ ምደባ ስድስት አዲስ ሆቴሎችን ጨምሮ 40 ሆቴሎች በኮከብ ደረጃ ውስጥ ገብተዋል።

ቀደም ሲል በኮከብ ደረጃ ውስጥ የነበሩ 15 ሆቴሎች ደግሞ በተለያዩ ምክንያቶች ኮከባቸው ተወስዷል።

የኮከብ ደረጃ ከተሰጣቸው ሆቴሎች መካከል 11 ሆቴሎች የባለ 5 ኮኮብ ደረጃ አግኝተዋል።

በተመሳሳይ 11 ሆቴሎች ባለ 4 ኮከብ ደረጃ ሲያገኙ፤ ዘጠኝ ሆቴሎች ባለ ሶስት፣ ሰባት ሆቴሎች ባለ ሁለት እንዲሁም 2 ሆቴሎች ባለ አንድ ኮኮብ ደረጃ ተሰጥቷቸዋል።

አሁን የተሰጠው ደረጃ ለሶስት ዓመት የሚያገለግል እንደሆነም ተገልጿል።

የተደረገው የሆቴሎች የደረጃ ምደባ የቱሪዝም ዘርፉን የሚደግፍና ቱሪስቶችን የሚስብ እንደሆነ ሲነሳ አሁን በአዲስ አበባ እየተስፋፋ የመጣውን የኮንፈረንስ ቱሪዝምን ያግዛል።

በዘመን በየነ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.