Fana: At a Speed of Life!

ትውልዱ ስለ ኢትዮጵያ የውኃ ሀብቶች እንዲገነዘብ ለማስቻል…

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ምሁራን አዲሱ ትውልድ ስለ ኢትዮጵያ የውኃ ሀብቶች ያለውን ግንዛቤ ለማሳደግ በትምህርት ሥርዓት መታገዝ አለበት አሉ፡፡

በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የውሃ ምህንድስና ክፍል መምህርና ተመራማሪ መኮንን አያና (ፕ/ር) ውኃ ህይወትና የብልጽግና መዳረሻ መሆኑን በመረዳት በልዩ ትኩረት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ተመራማሪው ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደተናገሩት፥ በሀገሪቱ የሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለዘርፉ ስኬታማነት በልዩ ትኩረት እየሠሩ ነው፡፡

የውኃ ሀብትን በዘላቂነት መጠቀም የሚያስችል አሠራር መዘርጋት አስፈላጊ መሆኑን የገለጹት ደግሞ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የውሃ ሀብትና የመስኖ ምህንድስና መምህር ሀብታሙ ኃይሉ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

መረጃ ላይ መሠረት ያደረገ የውኃ ሀብት አስተዳደርና ልማት እንዲኖር የተሟላ የተፋሰስ መረጃ ቋት ሊደራጅ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

ታላቁ ህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ የውሃ ሀብቷን ለልማት የተጠቀመችበት ትልቁ ማሳያ እንደሆነና የተጀመረውን ሁሉን አቀፍ የልማት ሥራ ከስኬት ለማድረስ የውኃ ሀብትን በአግባቡ መጠቀም ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ምሁራኑ እንዳሉት፥ መጪው ትውልድ ስለ ኢትዮጵያ ውኃ ሀብቶች ግንዛቤ ኖሮት እንዲያድግ በትምህርት ስርዓቱ ማገዝ ያስፈልጋል፡፡

በአስጨናቂ ጉዱ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.