Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ቴሌኮም የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለዕድለኞች በሽልማት አበረከተ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም ሁለት የኤሌክትሪክ መኪኖችን እና አምስት ባለሦስት እግር ተሽከርካሪዎችን ለዕድለኞች በሽልማት አበርክቷል።

130ኛ ዓመት ክብረበዓሉን ምክንያት በማድረግ ለደንበኞች የተለያዩ ሽልማቶችን እያበረከተ የሚገኘው ኢትዮ ቴሌኮም÷ በሁለተኛው ዙር ዕጣ ለወጣላቸው እድለኞች ሁለት ዘመናዊ የቢ.ዋይ.ዲ የኤሌክትሪክ መኪኖች እና አምስት ባለሦስት እግር ተሽከርካሪዎችን ማስረከቡን ገልጿል።

ኩባንያው ባለፉት 35 ሳምንታት ውስጥ ሁለት የኤሌክትሪክ መኪኖችን፣ ባለሦስት እግር ተሽከርካሪዎችን፣ ዘመናዊ ስማርት ስልኮችን ጨምሮ እስካሁን ከ75 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ሽልማቶች ለደንበኞች ማበርከቱን አመልክቷል።

በዛሬው ዕለትም ሁለት ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪኖችን እና አምስት ባለሦስት እግር ተሽከርካሪዎችን ዕጣ የማውጣት መርሐ ግብር በማካሄድ አሸናፊዎች መለየቱን ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በላከው መረጃ ገልጿል።

መርሐ ግብሩ እስከ ሰኔ 14 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚቆይ እና ደንበኞች አገልግሎቱን በመመዝገብ እየተጫወቱ ለተጨማሪ ሽልማቶች ባለዕድል እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.