Fana: At a Speed of Life!

ኢስትቫን ኮቫክስ የነገ ምሽቱን የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ይመራሉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አሊያንዝ አሬና ስታዲየም ነገ ምሽት የሚደረገውን የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ሮማኒያዊው ዳኛ ኢስትቫን ኮቫክስ በመሀል ዳኝነት ይመሩታል፡፡

የመሀል ዳኛው ኢስትቫን ኮቫክስ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ፣ ዩሮፓ ሊግ እና ኮንፈረንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታዎችን በመሀል ዳኝነት የመሩ የመጀመሪያው ሰው ይሆናሉ።

የ2024/25 የውድድር ዓመት የአውሮፓ ሻምፒንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ በፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ እና በጣሊያኑ ክለብ ኢንተር ሚላን መካከል ነገ ምሽት 4 ሰዓት ላይ በአሊያንዝ አሬና ስታዲየም ይደረጋል፡፡

ዋና ዳኛው ከዚህ በፊት ሁለት ጊዜ የፈረንሳዩን ክለብ ፒኤስጂን ጨዋታ በዳኝነት መርተው ፒኤስጂ ሁለቱንም ጨዋታዎች አሸንፏል፡፡

በሁለቱ ጨዋታ ዋና ዳኛው ለፒኤስጂ ተጫዋቾች አምስት የማስጠንቀቂያ ካርድ መምዘዛቸው ይታወሳል፡፡

በሌላ በኩል ኢስትቫን ኮቫክስ ሶስት ጊዜ የኢንተር ሚላንን ጨዋታ የመሩ ሲሆን ኢንተር ሚላን ምንም ሽንፈት አላስተናገደም፡፡

ኢንተር ሚላን ካደረጋቸው ሶስት ጨዋታዎች ሁለቱን ሲያሸንፍ በአንዱ አቻ ተለያይቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.