የመገጭ ግድብ ሥራ ፕሮጀክት ከነበረበት የአፈፃፀም ችግር መውጣት ጀምሯል – አብርሃም በላይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) የመገጭ ግድብ ሥራ ፕሮጀክት መንግስት በሰጠው ልዩ ትኩረት ከነበረበት የአፈፃፀም ችግር መውጣት ጀምሯል አሉ።
የፕሮጀክቱ አሁናዊ አፈፃፀም አብርሃም በላይ (ዶ/ር) በተገኙበት ተገምግሟል።
በዚህም ፕሮጀክቱ የቀደመው መሰረታዊ ችግሩ ተፈቶ አሁን ያለው አፈፃፀም ጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ታይቷል።
የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር)፤ ለዓመታት ግንባታው ሲጓተት የነበረው የመገጭ ግድብ ሥራ ፕሮጀክት መንግስት በሰጠው ልዩ ትኩረት ከነበረበት የአፈፃፀም ችግር መውጣት ጀምሯል ብለዋል።
በተደጋጋሚ ህዝቡ ሲያነሳ የነበረውን ጥያቄ መንግሥት በዘላቂነት ለመፍታት በወሰደው የፕሮጀክት አስተዳደር ለውጥ አሁን ላይ ፕሮጀክቱ ጥሩ አፈፃፀም ላይ ይገኛል ነው ያሉት፡፡
ፕሮጀክቱ በጥራትና በፍጥነት እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ ክትትል እየተደረገ እንደሆነም ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል።
ክረምት ከመግባቱ በፊት የፕሮጀክቱን የዘንድሮ ዕቅድ ለማሳካት በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
በምናለ አየነው