ሀዋሳ ከተማ መቻልን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ32ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሀዋሳ ከተማ መቻልን 3 ለ 1 አሸንፏል።
የሀዋሳ ከተማን ማሸነፊያ ግቦች አሊ ሱሌማን፣ ተባረክ ሄፋሞ እና አቤኔዘር ዮሐንስ አስቆጥረዋል።
መቻልን ከመሸነፍ ያልታደገውን ብቸኛ ግብ ምንይሉ ወንድሙ በፍጹም ቅጣት ምት አስቆጥሯል።
በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እየተካሄደ የሚገኘው የሊጉ መርሐ ግብር ሲቀጥል ምሽት 12:00 ላይ መቐለ 70 እንደርታ ከፋሲል ከነማ ይገናኛሉ።