Fana: At a Speed of Life!

ሀገር አቀፍ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ስትራቴጂን ለመተግበር እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአምራች ኢንተርፕራይዞችን የማምረት አቅም ማሳደግ የሚያስችል ሀገር አቀፍ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ስትራቴጂን ለመተግበር በትኩረት እየሰራሁ ነው አለ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት፡፡

የተቋሙ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሮቤል አሕመድ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ በአምራች ኢንተርፕራይዞች ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው፡፡

በተለይም በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የነባር አምራች ኢንተርፕራይዞችን አቅም የማጠናከርና አዳዲሶችን የማቋቋም ሥራ መሰራቱን አብራርተዋል፡፡

የብድር፣ የመስሪያ ቦታ፣ የኃይል አቅርቦትና እና ሌሎች ተግዳሮቶችን ተደራሽ ለማድረግ ከሚመለከታቸው አጋር አካላት ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ለዚህም የአምራች ኢንተርፕራይዞችን የማምረት አቅም ማሳደግ የሚያስችል ሀገር አቀፍ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ስትራቴጂን ለመተግበር ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡

ስትራቴጂው የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞችን ፍላጎትና ችግር መሰረት ያደረገ ጥናት በማካሄድ አስፈላጊውን ድጋፍ ለመስጠት ያለመ ነው ብለዋል፡፡

ይህም የአምራች ኢንተርፕራይዞችን የግብዓት፣ የፋይናንስ፣ የገበያ ትስስር፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና ሌሎች ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ሚናው ጉልህ እንደሚሆን ነው ያነሱት፡፡

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ስትራቴጂውን በፍጥነት ተግባራዊ ለማድረግም በሀገር አቀፍ ደረጃ ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.