Fana: At a Speed of Life!

የትግራይ ክልልን ተደራሽ ማድረግ የቀጣይ ሥራችን ነው- መስፍን አርዓያ (ፕ/ር)

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) ከሀገራዊ ምክክር አጀንዳ ማሰባሰብ ጋር በተያያዘ በቀጣይ የትግራይ ክልልን ተደራሽ ለማድረግ እንሠራለን አሉ፡፡

ምክክሩ አካታች እንደመሆኑ መጠን የትግራይ ክልልን ሳንይዝ የምክክሩ ስኬት የሚታሰብ አይደለም ነው ያሉት ዋና ኮሚሽነሩ፡፡

በመሆኑም የትግራይ ክልልን ተደራሽ ማድረግ በቀጣይ ኮሚሽኑ የሚያከናውነው ተግባር ነው ብለዋል፡፡

እንዲሁም በውጭ ሀገር ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋርም አጀንዳ የማሰባሰብ መርሐ ግብር ይከናወናል ነው ያሉት፡፡

በሌላ በኩል በትጥቅ ትግል ላይ ያሉ ወገኖች አጀንዳዎቻቸውን ወደ ምክክር ቋቱ እንዲያስገቡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዛሬ የተጠናቀቀው የፌደራል ተቋማት እና ማኅበራት አጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት አጀንዳ ርክክብ፤ ተቋማቱ የተዋሐደ አጀንዳዎችን ማቅረብ የቻሉበት መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በይስማው አደራው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.