ማንቼስተር ዩናይትድ ማቲውስ ኩንሀን አስፈረመ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ማንቼስተር ዩናይትድ ብራዚላዊውን የፊት መስመር ተጫዋች ማቲውስ ኩንሀን ከወልቭስ ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል፡፡
የ26 ዓመቱ ማቲውስ ኩንሀ በማንቼስተር ዩናይትድ ቤት በፈረንጆቹ እስከ 2030 የሚያቆውን ውል ፈርሟል፡፡
ከአምሥት ዓመት ውሉ ባሻገር ለአንድ ዓመት የማራዘም ተጨማሪ አማራጭ መኖሩ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ተጠቅሷል፡፡
ዩናይትድ ለማቲውስ ኩንሀ ዝውውር 62 ነጥብ 5 ሚሊየን ፓውንድ ለወልቭስ ከፍሏል፡፡
አዲሱ የቀያይ ሰይጣኖቹ ፈራሚ ማቲውስ ኩንሀ 10 ቁጥር መለያ እንደሚለብስ ተገልጿል።