Fana: At a Speed of Life!

ኦስማን ዴምቤሌ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተመረጠ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፈረንሳዊው የፒኤስጂ የፊት መስመር ተጫዋች ኦስማን ዴምቤሌ የ2024/25 አውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የውድድሩ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተመርጧል፡፡

የ28 ዓመቱ ዴምቤሌ በውድድር ዓመቱ ባደረጋቸው 15 የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች፤ 8 ጎል አስቆጥሮ 6 ለግብ የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል፡፡

ፒኤስጂ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ሲያሳካ የዴምቤሌ አስተዋፅኦ የጎላ ነበር፡፡

ፒኤስጂ በፍፃሜው ኢንተርሚላንን 5 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ  ሻምፒየን መሆኑ ይታወቃል፡፡

በፍፃሜው ጨዋታ ሁለት ጎል አስቆጥሮ አንድ ለግብ የሚሆን ኳስ አመቻችቶ ያቀበለው ሌላኛው የፒኤሴጂ ተጫዋች ዱዌ የዓመቱ ምርጥ ወጣት ተጫዋች በመባል መመረጥ ችሏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.