Fana: At a Speed of Life!

የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድቦች ኃይል ለማመንጨት የሚያስችላቸውን በቂ ውኃ ይዘዋል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሁሉም የኃይል ማመንጫ ግድቦች በበጀት ዓመቱ የታቀደውን ኃይል ማመንጨት የሚያስችላቸውን በቂ የውኃ መጠን ይዘዋል አለ፡፡

የተቋሙ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስኪያጅ ፍስሐ ጌታቸው ለፋና ዲጂታል እንደገለጹት፤ 14 የውኃ ኃይል ማመንጫ ግድቦች እስከ ሰኔ 30 ቀን 2017 ድረስ ለማመንጨት የታቀደውን ኃይል ማሳካት የሚያስችል በቂ የውኃ መጠን ይዘዋል፡፡

በአሁኑ ወቅትም ጊቤ lll፣ በለስ፣ ገናሌ ዳዋ 3፣ ተከዜ፣ ግልገል ጊቤ l ፣ ፊንጫ፣ መልካ ዋከና፣ ነሼ፣ ጢስ ዓባይ l ፣ ቆቃ፣ እና ሌሎችም ኃይል ማመንጨት የሚያስችላቸውን እና መያዝ የሚጠበቅባቸውን ውኃ ኃይል መያዛቸውን አረጋግጠዋል፡፡

የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድቦቹ ውኃ የመያዝ አቅም ከ74 ሺህ 500 እስከ 448 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ መሆኑን ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ጊቤ ll ከጊቤ l፣ ጢስ ዓባይ ll ከጣና ሐይቅ፣ አዋሽ ll እና lll ከቆቃ የሚጠቀሙ ወይም የራሳቸው ግድብ የሌላቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.