አዳማ ከተማ ባሕር ዳር ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ33ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር አዳማ ከተማ ባሕር ዳር ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡
የአዳማ ከተማን የማሸነፊያ ግቦች ቢንያም አይተን እና ሙሴ ኪሮስ በሁለተኛው አጋማሽ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
አዳማ ከተማ ተከታታይ ሶስተኛ ድሉን ያሳካ ሲሆን÷በአንጻሩ ባሕር ዳር ከተማ ሶስት ተከታታይ ጨዋታዎችን ተሸንፏል፡፡
ውጤቱን ተከትሎ ባሕር ዳር ከተማ በ48 ነጥብ 3ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ አዳማ ከተማ ደግሞ በ35 ነጥብ 15ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
የሊጉ መርሐ ግብር ሲቀጥል ምሽት 12 ሰዓት ላይ አርባ ምንጭ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡