Fana: At a Speed of Life!

የቻይና ቀዳማዊት እመቤት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር የሚረዱ ቁሳቁሶችን ለኢትዮጵያ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 4 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቻይና ቀዳማዊት እመቤት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር የሚያግዙ ቁሳቁሶችን አበረከቱ።

ቀዳማዊት እመቤት ፒንግ ሊዋን የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር ቁሳቁሶችን ማበርከታቸውንም የኢትዮጵያ ቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት ባወጣው መረጃ አስታውቋል።

የቻይና ቀዳማዊት እመቤት ለኢትዮጵያ ያበረከቱት ድጋፍም 18 ሺህ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛዎችን እንዲሁም 120 የሙቀት መለኪዎችን መሆናቸውንም ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.