ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ድሬዳዋ ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ33ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ድሬዳዋ ከተማን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
የወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ሱልጣን በርሄ፣ ናትናኤል ሰለሞን እና ዳዊት ገብሩ አስቆጥረዋል፡፡
ድሬዳዋ ከተማን ከሽንፈት ያልታደገች ብቸኛ ግብ ዘርዓይ ገብረሥላሴ ከመረብ አሳርፏል፡፡
ድሬዳዋ ከተማ ከሦስት ተከታታይ ጨዋታዎች ድል በኋላ ሽንፈት አስተናግዷል፡፡
የሊጉ ጨዋታ ሲቀጥል ምሽት 12 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ መድን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ መድን የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ ከቻለ ቀሪ ሦስት ጨዋታዎች እያሉ ሻምፒዮን መሆኑን ያረጋግጣል፡፡