የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብልፅግና ፓርቲ በወቅታዊ ክልላዊና ሀገራዊ ለውጥ ዙሪያ እየመከረ ነው
አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 4 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብልፅግና ፓርቲ በወቅታዊ ክልላዊ ፀጥታ፣ ልማትና ሀገራዊ ለውጥ ዙሪያ ውይይት እያደረገ ይገኛል፡፡
በውይይቱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰንን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልጽግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢስሃቅ አብዱልቃድርም ሰነዱን እያቀረቡ ይገኛሉ።
አመራሮቹ በአጀንዳዎቹ ዙሪያ ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሁለት ቀናት ግምገማ እንደሚያካሂዱ ታውቋል፡፡
ከተወያዩ በኋላም ውሳኔዎችንና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።