Fana: At a Speed of Life!

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ በተከናወኑ ሥራዎች አበረታች ውጤት ተመዝግቧል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የተያዘውን ራዕይ እውን ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ተጨባጭ ውጤት እየተመዘገበ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን በጥራት መንደር ውስጥ የተረከበው ሕንጻ ተመርቋል፡፡

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የተያዘውን ራዕይ እውን ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ተጨባጭ ውጤት እየተመዘገበ ነው።

የጥራት መንደሩ ለኢኮኖሚ ዕድገት ጉልህ አስተዋጽዖ እንዳለው ጠቅሰው፤ መንደሩ ለኢኮኖሚ ዕድገት ወሳኝ የሆኑ ተቋማት በቅንጅት የሚሠሩበት ነው ብለዋል፡፡

ይህም ኢትዮጵያን በአፍሪካ በጉልህ የሚያስጠቅሳት መሠረተ ልማት ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የጥራት መንደር የኢትዮጵያን የልማት መሻት የዋጀ የነገ ፍላጎት ማሳያ እንዲሁም ለትውልድ የሚተርፍ ጸጋ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

የተረከቡት ሕንጻ ባለስልጣኑ የተሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ መወጣት የሚያስችለው መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሰለሞን ጌታቸው ናቸው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.